በማኅበረሰብ-ተኮርማገገሚያውስጥያሉአጋሮች

የጎንደርእናየኩዊንስዩኒቨርሲቲካናዳበሚገኘውዓለማቀፋዊየተራድኦድርጅትማስተርካርድፋውንዴሽንድጋፍአማካኝነትለሚቀጥሉትአስርዓመታትበአካልጉዳተኛወጣቶችንተጠቃሚየሚያደርግከፍተኛትምህርትንለማስፋፋት፤አዳዲስየሙያላይህክናፕሮግሞችንለማዘጋጀትእናየማህበረሰብ-ተኮርማገገሚያምርምርበጋራለመስራትተስማምተዉስራዉተጀምሯል።

ስለ እኛ አጋርነት ተጨማሪ ለማወቅ

ስለ ብቁነት መስፈርቶች ተጨማሪ ይወቁ [ስለ ነጻ ትምህርት ፕሮግራም ብቁነት ማገናኛ ገጽ]

ዜና

የባለ ድርሻ አካላት ማነቃቂያ ስብሰባ ታህሳስ 3፣ 2010 በአዲስ አበባ ተካሄደ

በጎንደር ዩኒቨርቲና በኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ስኮላርስ ፕሮግራም የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፕሮግራምን ለመጀመር የባለ ድርሻ አካላት ማነቃቂያ ስብሰባ ታህሳስ 3፣ 2010 በአዲስ አበባ አካሄደ፡፡

Read More
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማስተርካድ ተማሪዎችን ተቀበለ፡-ለአካል ጉዳተኞች ብሩህ መንገድ ከፈተ

የማስተርካርድ ስኮላርስ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀበለ፡፡ ቀኑ በአቀባበልና በምዝገባ ጀምሮ ወጣት አዋቂዎቹን ለሰፊዉ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብና እንደ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ለወደፊት የሚጠብቃቸዉን ጠቅላላ ጉዞ አሰተዋዉቋል፡፡

Read More
ከአጋር አካላትና ባለድርሻዎች ጋር አስተዳደራዊ ስብሰባ ተደረገ ህዳር 24፡ 2010 ዓ.ም

በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ ሲ. ቢ. አር ቢሮ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ፕሮግራም የግለ-ግምገማ መድረክ አካሄደ፡፡

Read More

ስለዚህ ፕሮጀክት

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሃገራችን በቀዳሚነት የጤና ሙያተኞችን ለማፍራት የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ኮሌጅና ማሰልጠኛ ማዕከል በሚል ስያሜ በ1947 ዓ.ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ተመሰረተ። በሀገራችን የጤና ሙያተኞችን ለማሰልጠን በቀዳሚነት የተቋቋመው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአመሰራረቱ ጀምሮ በሂደት በተለያዩ ስያሜዎች በእድገት ጎዳና እየተጓዘ ዛሬ በሀገራችን ከሚገኙት ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መሰለፍ የቻለ፤ በርካታ ታዋቂ ምሁራንን ለሀገር በማበርከት አኩሪ ታሪከዊ ረጅም ጉዞ የተጓዘና በመማር ማስተማሩ፤ በምርምሩና በማህበረስብ አገልግሎቱ ውጤታማ ተግባር ያከናወነ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሀገር ዕድገትና ለህዝቦች ኑሮ መሻሻል ፋይዳ ባላቸው የትምህርት መስኮች በአንደኛ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ትምህርት ይሰጣል፤ የህብረተሰብ ችግር ፈቺ ምርምር ያካሂዳል፡፡ በአሁኑ ሰአት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን ድጋፍ ለ450 ወጣቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ይሰጣል። እንዲሁም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና እና የምርምር እድሎችን ያመቻቻል።

አጋሮቻችን

የጎንደር ዩኒቨርስቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሃገራችን በቀዳሚነት የጤና ሙያተኞችን ለማፍራት የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ኮሌጅና ማሰልጠኛ ማዕከል በሚል ስያሜ በ1947 ዓ.ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ተመሰረተ።ዩኒቨርስቲው 70 የቅድመ ምረቃ እና 90 ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ይሰጣል።

ስለ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተጨማሪ ይወቁ

ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ

ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ በካናዳ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በግምባር ቀደም ተጠቃሽ ዩኒቨርስቲ ሲሆን ፤ የተመሰረተበትን 175 ኛ ዓመት በማክበር ላይ ይገኛል። የዩኒቨርሲቲው ህክምናና ጤና ሳይንስ ፋካሊቲ የተሀድሶ ህክምና ትምህርት ቤት, የነርስ ትምህርት ቤት እና የህክምና ትምህርት ቤት ያካትታል።

ስለ ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲተጨማሪ ይወቁ

ስፖንሰርዎቻችን

የ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የትምህርት ፕሮግራም

የማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጠንካራ ከሚባሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተለይ በአፍሪካ በዋነኝነት በድህነት የሚኖሩ ሰዎች ትምህርት ተደራሽነት እንዲኖረው ይሰራል, የሙያ ስልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። ከዋና ዋናዎቹ ዓለማቀፋዊ የተራድኦ ድርጅት አንዱ ሲሆን እንደ ዋና ተልእኮ የተሻለ ትምህርት እና የፋይናንስ ተሳትፎ በማበረታታት ድህነትን ለማቃለል ይሰራል።

ስለ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የትምህርት ፕሮግራሞች ተጨማሪ ይወቁ